. እንኳን ደህና መጡ
ተስፋ ሕይወት ሰንበት
ትምህርት ቤት
የወልቂጤ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ተስፋ ሕይወት ሰ/ት/ቤት በ1990 ዓ.ም ተመሰረተ ።
. ተስፋሕይወት
"እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ" ማቴ 28÷20
በ1991ዓ.ም አባ ፍስሀ ተ/ጽዮንን በመያዝ ቤት ለቤት በመዞርከ ምዕመናኑ በተሰበሰበው ገንዘብ 20 የወጣቶች እና 10 የህፃናት ልብሰ ስብሐት በማሰፋት ለአገልግሎት አብቅተዋል ።
ተስፋ ሕይወት
ከ 1990 ዓ.ም
ጀምሮ
ሰ/ት/ቤት ማለት በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ወጣቶች እና ህፃናት ስለ ሃይማኖታቸው ስርአት ፣ ዶግማ ፣ ትውፊት እና ታሪክ የሚማሩበት እና እራሳቸውን በመንፈሳዊ ህይወት የሚያንፁበት አና መልካም ፍሬን የሚያፈሩበት ተቋም ነው።
ስለ ሰንበት ት/ቤቱ መሰረታዊ መረጃዎች
ሰንበት ትምህርት ቤቱ 2022 ዓ.ም በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ከሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በትምህርት አሰጣጥ እና በአባላት ስነ ምግባር በግንባር ቀደምነት የሚጠቀስ ሰንበት ትምህርት ቤት ሆኖ ማየት ።
- በአጥቢያው የሚገኙ ወጣቶች እና ህፃናት ትክክለኛውን ትምህርተ ሃይማኖት እና የአብነት ትምህርትን በማስተማር የቤተክርስትያኗን ዶግማ ፣ትውፊት ፣ ቀኖና ፣ ስርአት እና ታሪክ እንዲያውቁ ማድረግ፡፡
- የሰ/ት/ቤቱ አባላት በመናፍቃን እንዳይነጠቁ አስፈላጊውን እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ፡፡
- የተለያዩ መንፈሳዊ ጉባዬዎችን በማዘጋጀት ለምዕመኑ ቃለ እግዚአብሔርን ማስተማር ፡፡
- በቤተክርስቲያኑ ውስጥ በሚደረጉ ልዩ ልዩ መርሀ ግብራት ላይ በመሳተፍ የቤተክርስቲያኑን አገልግሎት ማገዝ ፡፡
- አባላቱ በሰ/ት/ቤቱ ውስጥ ባሉ ክፍላት ላይ በመሳተፍ መክሊታቸውን እንዲያተርፉበት ማድረግ፡፡
- ሕፃናት እና ወጣቶችን የቤተክርስትያንን ሚስጥራትን በማስተማር የሚስጢር ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል።
- መንፈሳዊ ወጣቶች እና ህፃናት የቤተክርስትያንን እና የሀገርን ታሪክ በሚገባ አውቀው በነገረ
መለኮት ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ተምረው የነገዋን ቤተክትስትያን እና ሀገርን በሃላፊነት ለመረከብ
ብቁዎች ማድረግ ፡፡
- ከስብከተ ወንጌል ፣ ከካህናት እና ከተለያዩ አባላት ጋር ተባብሮ በመስራት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ
ሃይማኖት ፣ ስርአት እና ትውፊት ሳይበረዝ እና ሳይለወጥ ከተውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ
ማድረግ ፡፡
- የሰ/ት/ቤቱ አባላት ያላቸውን መክሊት (ፀጋ) ተጠቅመው ቤተክርስትያንን እንዲያገለግሉ ማድረግ
- ወጣቶች እና ህፃናት የሃይማኖታቸውን ስርአት ፣ ትውፊት እና ዶግማ እንዲያውቁ ፤በስነምግባራቸውም የታነጹ እና ክርስትያናዊ ግብረገብ የተላበሱ እንዲሆኑ ማድረግ ፡፡
- ሃይማኖታቸውን አፅንተው እንዲይዙና እንዲጠብቁ ማድረግ ፡፡ 2ኛ ጢሞ 4፥7-8 "ሃይማኖቴን
ጠብቄአለሁ ወደ ፊት የፅድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል "

የመምህራን ግንዛቤ ማስጨበጫና የትምህርት ማስጀመሪያ ውይይት
ተስፋሕይወት ሰንበት ት/ቤትሽ በአንቺ ትኮራለች!
የአዲስ ዓመት በዓል በተስፋሕይወት ሰ/ት/ቤት በድምቀት ተከበረ።
