ስያሜ
በጉራጌ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ወረዳ
የወልቂጤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን
የወልቂጤ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እስከ 2016 ዓም ድረሰ ደብረ ሲና ቅዱስ ገብርኤል ሲባል ቆይቶ በ2016 ዓ.ም በሀገረ ስብቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ መልከፄዴቅ ሣልሳይ አማካኝነት የደብሩ ስያሜ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ተብሎ ተሰይሟል።
በደብሩ የሚከበሩ የንግሥ በዓላት
ታህሳስ 19 የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግሥ
አዛርያ፣ አናንያ እና ሚሳኤል የተባሉ ሦስት ሕፃናት ከእቶን እሳት ያዳነበት ክብረ በዓል ነው።
የካቲት 16 የቅድስት ኪዳነምህረት በዓለ ንግሥ
ቅድስት ኪዳነምህረት የምህረት ቃል ኪዳንን የተቀበለችበት ዓመታዊ ክብረ በዓሏ ነው።
ሚያዝያ 23 የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ንግስ
የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ንግስ
ሰኔ 30 መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የተወለደበት ዕለት ነው
ሃምሌ 19 የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግሥ
አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣ ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው።
ነሃሴ 16 የእመቤታችን በዓለ ዕርገት
የእመቤታችን በዓለ ዕርገት የሚታሰብበት ዕለት ነው
የስብከተ ወንጌል መርሃግብራት
ስብከተ ወንጌል
- ዘወትር ሀሙስ ሳምንታዊ ልዩ ጉባኤ(ተታታይ መሠረታዊ የቤተክርሰቲያን ትምህርት)
- መደበኛ የየዕለት የሰርክ ጉባኤያት(ዓመቱን ሙሉ)
- ታላላቅ ልዩ ጉባኤያት በየ3 ወሩ
- ለአጥቢያው አገልጋዮችና ምዕመናን ልዩ ልዩ ስልጠናዎች
- የአብነት ትምህርት(በሁለት የአብነት መምህራን)
የልማት ስራዎች