የሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት
በጽሕፈት ቤቱ ስር ሰብሳቢ፣ምክትል ሰብሳቢና ጸሐፊ ይኖራሉ፡፡
ሰብሳቢ
- የሰንበት ትምህርት ቤቱን የአባላትና የስራ አስፈጻሚ ጉባኤ ስብሰባ ይመራል፡፡
- ከሰበካ ጉባኤ ጽሕፈት ቤትና ከሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን ያሳውቃል፣ያስፈጽማል፡፡
- በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ሰንበት ትምህርት ቤቱን ወክሎ ይገኛል ፤ ካልተገኘም ሌሎች የስራ አስፈጻሚዎችን መወከል ይችላል፡፡
- በስብሰባ ጊዜ ድምጽ እኩል ሲሆን ሰብሳቢው የወሰነው ውሳኔ ይጸድቃል፡፡
- ሰንበት ትምህርት ቤቱን ወክሎ የተለያዩ ውሎችን ይዋዋላል፡፡
- ከጸሐፊው ጋር በመነጋገር አጀንዳዎች እንዲያዙ ያደርጋል፡፡
- ወደ ሰንበት ትምህርት ቤቱ የሚመጡ ደብዳቤዎችን ተቀብሎ ምላሽ ይሰጣል፤ይመራል፡፡
- በከፍተኛ የሒሳብ ሰነዶች ላይ ይፈርማል፡፡
- እስከ አንድ ሺ ብር ወጪ እንዲያደርግ ጸሐፊውን መወከል ይችላል፡፡
- ዓመታዊ እቅዶችን ተወያይቶ ያጸድቃል ፡፡
የወቅቱ የሰንበት ት/ቤቱ ሰብሳቢ፡
ሳህለጊዮርጊስ ተስፋዬ
ምክትል ሰብሳቢ
- ሰብሳቢው ባልተገኘበት ጊዜ ሙሉ የሰብሳቢውን ሀላፊነት ይወስዳል፡፡
- ሰብሳቢው የሚሰራውን ስራ ያግዛል፡፡
- የጽሕፈት ቤቱን እንቅስቃሴ ይከታተላል፡፡
የወቅቱ የሰንበት ት/ቤቱ ም/ሰብሳቢ፡
አዲሱ መኳንንት
ጸሐፊ
- ከሰብሳቢው ጋር ሆኖ አጀንዳ ያዘጋጃል
- በሰንበት ትምህርት ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤና በስራ አስፈጻው ጉባኤ ስብሰባ ላይ ቃለ ጉባኤ ይይዛል፤ ያስፈርማል፡፡
- እቅዶችን በማስታወስ ተፈጻሚ ያደርጋል፡፡
- ሰብሳቢውና ምክትል ሰብሳቢው በማይገኙበት ጊዜ ወክሎ ይሰራል፡፡
- የስራ አስፈጻሚውን ውሳኔ ለሚመለከተው አካል በቃልና በጽሑፍ ያሳውቃል፡፡
- የሰንበት ትምህርት ቤቱን ገቢና ወጪ ደብዳቤ በአግባቡ ይቆጣጠራል፤ ይሰንዳል ፡፡
- የጽሕፈት ቤቱን ንብረቶች በአግባቡ ይይዛል ጉድለቶቹን አጥንቶ፤ ግዢ እንዲፈጸም ያደርጋል፡፡
- ወደ ሰንበት ትምህርት ቤቱ የሚመጡ እንግዶችን ያስተናግዳል፤ጉዳያቸውን ያስፈጽማል፡፡
- ደብዳቤዎችን ያዘጋጃል፤ የሰንበት ትምህርት ቤቱን አሰራር የሚያፋጥኑ ልዩ ልዩ ቅጾችን ያዘጋጃል፡፡
- በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤና በሰንበት ትምህርት ቤቱ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ዓመታዊ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፡፡
- በስብሰባ ጊዜ ሰብሳቢው በተወሰነው ጊዜ ጀምሮ እንዲፈጽም ያደርጋል (የስብሰባ ሰዓት ይቆጣጠራል) ፡፡
- ሰብሳቢው ውክልና ሲሰጠው እስከ 1000 ብር ወጪ ማድረግ ይችላል፡፡
- የክፍላት ተጠሪዎች ዕቅድ ና ሪፖርት በጊዜው እንዲያስገቡ ያደርጋል፡፡