መዝሙር ክፍል
- በሰንበት ትምህርት ቤቱ የሚዘጋጁና የሚቀርቡ ዝማሬዎችን ከዝግጅት አንስቶ እስኪቀርቡ ድረስ ይከታተላል፡፡
- በስሩ አራት ንኡስ ክፍላትን ይይዛል
አምሳል ለማ
የወቅቱ የክፍሉ ተጠሪ
መዝሙር ጥናት ንኡስ ክፍል
- በዓመት ውስጥ የሚቀርቡ መዝሙራትን ለየወቅቱ ከፋፍሎ ያቅዳል፡፡
- መዝሙሮቹን በጽሑፍና በድምጽ ያዘጋጃል (የግእዝ መዝሙሮችን ከነ ትርጓሜያቸው)፡፡
- መዝሙር አስጠኚዎችን ይመድባል፡፡
- የታቀዱት መዝሙሮች በአግባቡ መጠናታቸውን እና መቅረባቸውን ይከታተላል፡፡
- ከስርአተ ቤተክርስቲያን ውጪ የሆኑ ዝማሬዎችን ይለያል፡፡
ወረብ ጥናት ንኡስ ክፍል
- በዓመቱ የሚቀርቡ ወረቦችን ለይቶ ያወጣል፤ ያቅዳል፣ ያስጠናል(ከነ ትርጓሜያቸው)፡፡
- ወረብ አሰስጠኚዎችን ይመድባል፤ ከመምህራን ጋር እንዲገናኙ ያደርጋል፡፡
- ወረብ ጥናቶችን ይከታተላል ይገመግማል፡፡
- ለጥናቱ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ያዘጋጃል፡፡
የግል ዝማሬ ንኡስ ክፍል
- አውደ ምህረት ላይ እና የሰንበት ትምህርት ቤት መርሀግብር ላይ በግል የሚዘምሩ(መዘመር የሚችሉ) አገልጋዮችን ይመርጣል፡፡
- ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ወደ ሌላ አካባቢ የሚላኩ ዘማርያንን ይመርጣል ፤ይወክላል፡፡
- በሰርክ ጉባኤ የሚዘምሩ አገልጋዮችን ፣ይመርጣል እንዲሁም መርሀግብር ያወጣል፡፡
- ስልጠናዎችን አዘጋጅቶ እንዲሰለጥኑ ያደርጋል(ከትምህርት ክፍሉ ጋር በጋራ በመሆን)
የዜማ መሳሪያ ስልጠና ንኡስ ክፍል
- የዜማ መሳሪያ ስልጠና ያዘጋጃል
- አሰልጣኞችን ይፈልጋል
- የዜማ መሳሪያ ግዢ እንዲፈጸም ያደርጋል
- ስልጠና የጨረሱ አባላትን በልዩ ልዩ አገልግሎቶች ላይ ያሳትፋል፡፡
error: