Tesfahiwot

ልማትና በጎ አድራጎት ክፍል


  • በሰንበት ትምህርት ቤቱ ውስጥ እና ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ውጭ የልማትና የበጎ አድራጎት ስራዎችን ያከናውናል፡፡
  • በቤተክርስያኑ ውስጥ በሚከናወኑ የልማት ስረዎች ላይ እገዛ ያደርጋል፡፡
  • በስሩ አራት ንኡሳን ክፍላት ይኖራሉ፡፡


  • በሰንበት ትምርት ቤቱ ውስጥ የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው አባላትን ይለያል፡፡
  • በሰንበት ትምህርት ቤቱ ውስጥ የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው አባላት ድጋፍ ያደርጋል፡፡
  • አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
  • እራሳቸውን ማሻሻል እንዲችሉ የገቢ ማስገኛ መፍትሄዎችን ይቀርጻል፡፡
  • ከአባላት የቁሳቁስና የገንዘብ እርዳታ ይሰበስባል፣ልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ዘዴዎችን ይቀርጻል፡፡

  • ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ውቺ ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች እርዳታ ያደርጋል፡፡
  • በበዓላትን በልዩ ልዩ ጊዜያት ነዳያንን ይመግባል፣ድጋፍ ያደርጋል፡፡
  • አልባሳትና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ ያደርጋል፡፡
  • እስረኞችን እና ህመምተኞችን ይጎበኛል፤ አቅመ ደካሞችን በጉልበትና በገንዘብ ያግዛል፡፡

  • በየጊዜው የሰንበት ትምህርት ቤቱን ገቢ ለማሳደግ ልዩ ልዩ ፕጀክችን ይቀርጻል፡፡
  • የሰንበት ትምህርት ቤቱን ሱቅና ሌሎች የገቢ ምንጮችን ይከታተላል፡፡
  • ለሽያች የሚቀርቡ ንዋያትን ያስመጣል፡፡

  • በደብሩ ቅጥር ግቢ ውስጥና በሰንበት ትምህርት ቤቱ ያሉ ልማታዊ ስራዎችን ያግዛል፡፡
  • የችግኝ ተከላ መርሀግብሮችን ያዘጋጃል፣ይተክላል፣ ይንከባከባል፡፡
  • ግንባታዎች ሲኖሩ አባላትን በማስተባበር የጉልበት እገዛ ያደርጋል፡፡
  • የደብሩን ቅጥር ግቢ እና ቤተ መቅደሱን በየጊዜው ያጸዳል፡፡
  • ልብሰ ተክህኖ፣የካህናት ልብስ እንዲታጠብ፣የካህናት ቤት እንዲጸዳ ያደርጋል፡፡
error: