ኪነጥበብ ክፍል
- በሰንበት ትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚከወኑ ኪነጥበባዊ መርሀግብራትን ሁሉ በስሩ ይመራል፡፡
- ከሰንበት ትምህርት ቤት ውጪም ለምእመናን ኪነ ጥበባዊ መርሀግብራትን ተደራሽ ያደርጋል፡፡
- በስሩ አራት ንኡሳን ክፍላት ይኖራሉ
የውስጥ መርሀ ግብራት አስተባባሪ ንኡስ ክፍል
- በሰንበት ትምህርት ቤቱ ውስጥ ለአባላት የእሁድ መርሀግብራትን ያዘጋጃል፡፡
- በሰንበት ትምህርት ቤቱ ውስጥ ልዩ መርሀግብራት ሲኖሩ ኪነጥበባበዊ መርሀግብራትን ያቀርባል፡፡
- የኪነ ጥበብ ስልጠና ይሰጣል፡፡
- በየጊዜው በክፍሉ የሚቀርቡ ኪነጥበባዊ መርሀግብራትን ወደ ኮምፒተር ይገለብጣል ፕሪንት ያደርጋል፡፡
የውጭ መርሀ ግብራት
- የስነጽሑፍ ምሽቶችንና ቲያትሮችን አዘጋጅቶ ያቀርባል፡፡
- በደብሩ በሚከበር በዓለ ንግስ ላይ፣በጥምቀትና…ወዘተ አዳር መርሀግብራትን ያዘጋጃል፡፡
- ጉባኤያት እንዲሁም በዓላት ሲኖር በአውደምህረት የሚቀርቡ መርሀግብራትን አዘጋጅቶ ያቀርባል፡፡ በየጊዜው በክፍሉ የሚቀርቡ ኪነጥበባዊ መርሀግብራትን ወደ ኮምፒተር ይገለብጣል ፕሪንት ያደርጋል፡፡
ስነ ስዕል ንኡስ ክፍል
- በየደረጃው ላሉ የበሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት ኦርቶዶክሳዊ የሥነ ስዕል ስልጠና ይሰጣል፡፡
- የስእል አውደ ርእይ ያዘጋጃል፡፡
- የተሳሉትን ስእሎች በአግባቡ ያስቀምጣል፡፡
- ለስዕል የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ያሟላል፡፡