Tesfahiwot

አባላት ጉዳይ ክፍል


  • የአባላትን ጉዳዮች ይከታተላል
  • የሰንበት ትምህርት ቤቱን ግንኙነት ያጠናክራል፡፡
  • በስሩ አምስት ንኡሳን ክፍላት ይኖሩታል


  • የንስሀ አባት የሌለቸውን እና ያላቸውን አባላት ይለያል
  • የንስሀ አባት የሌላቸውን አባላት ከአባቶች ጋር እንዲገናኙ ያደርጋል፡፡
  • የንስሀ ትምህርት ይሰጣል
  • የወንድሞች እና የእህቶች ጉባኤ
  • በየጊዜው የሕይወት ውይይቶችን ያዘጋጃል፡፡
  • መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ይከታተላል፣ዝለት ለታየባቸው አባላት የምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡
  • በሀዘን እና በደስታ ጊዜ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፡፡
  • የቤተሰብ መዋቅሩን ይመራል, ይከታተላል።

  • ለሁሉም ክፍላት ቋሚ የጸሎት ሥርዓት ያዘጋጃል
  • ጸሎት የሚያሳርጉ አገልጋዮችን ይመድባል
  • ወቅታዊ የጸሎት መርሃግብራትን ይቀርጻል
  • ለአባላት የጸሎት ሕይወታቸውን እንዲያሳድጉ ልዩ ልዩ እገዛዎችን ያደርጋል
  • የሰንበት ትምህርት ቤቱን የዓመት ቋሚ የጸሎት መርሃግብር ያወጣል
  • መርሃግብር ቀርጾ የሕብረት ጸሎት የሚደረግበትን መንገድ ለአባላት ያሰለጥናል (ያሳውቃል
  • ለጸሎት የሚያስፈልጉ ግብአቶቸን (ቁሳቁሶችን…) ያሟላል
  • ሰንበት ትምህርት ቤቱ ፈተና በገጠመው ጊዜ አባቶች(ገዳማውያን) ጸሎት እንዲይዙለት ያስተባብራል
  • ሁሉም ክፍላት የጋራ የጸሎት ቀን እንዲኖራቸው ያደርጋል
  • የሌሎች ሰንበት ት/ት ቤቶችን የጸሎት ልምድ ይካፈላል

  • አዳዲስ አባላትን አስቀድሞ ያገኛል መሰረታዊ መረጃዎችን ያሳውቃል፡፡
  • አዳዲስ አባላትን ይከታተላል፣ያወያያል፣ይደውላል..ወዘተ፡፡
  • መርሀ ግብሮችን ያሳውቃል፡፡
  • ከነባር አባላት ጋር ያስተዋውቃል፡፡
  • ለአገልግሎት የደረሱ አባላትን ፎርም ያስሞላል፡፡
  • ለአገልግሎት የደረሱ አባላትን ለቁጥጥር ክፍሉ ያስተላልፋል፡፡
  • በየጊዜው የጠፉ አባላትን ይፈልጋል፡፡
  • ጠፍተው የተመለሱ አባላት ወደ ቀድሞ አገልግሎታቸው እንዲመለሱሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡
  • የአባላት መመዝገቢያ ፎርም ያዘጋጃል
  • የአባላትን ፎርም በአግባቡ ይሰንዳል፣ ያደራጃል፡፡

  • የሰንበት ትምህርት ቤቱን የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮችንና ሌሎች የግኑኝነት መስመሮችን በስሩ ይቆጣጠራል፡፡
  • ሰንበት ትምህርት ቤትን የሚመለከቱ መረጃዎችን ይሰበስባል ያሳውቃል፡፡

  • በሰንበት ት/ት ቤት ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ክፍሎች ላይ የየክፍሉን የስም ቁጥጥር የሚያደርግ ሰው ይመርጣል።
  • የአባለትን መገኘት ይቆጣጠራል (ስም ይጠራል)
  • በየጊዜው ቀሪ የሚያበዙና የጠፉ ልጆችን ስም ዝርዝር ለአዳዲስ አባላት ንኡስ ክፍል ያስተላልፋል፡፡
  • ለበዓላት የሚዘምሩ/የሚያቀርቡ ዘማርያንን ይመርጣል።

  • ለአገልግሎት የሚሆን የሰው ኃይል ያበቃል
  • ከጽ/ቤት ጋር በመሆን ለአገልግሎት የሚሆኑ አባላትን ያሰለጥናል
  • ለአገልግሎት የሚሆን የሰው ኃይል ወደ ክፍላት ይመድባል
  • ከክፍላት ወደ ክፍላት የሚደረግ ዝውውር በዚህ ክፍል ይፈጸማል
  • እንዳስፈላጊነቱ ከክፍላት ተጠሪዎች ጋር በመነጋገር ከክፍላት ወደ ክፍላት አባላትን ያሸጋሽጋል
error: