ልማትና በጎ አድራጎት ክፍል
- በሰንበት ትምህርት ቤቱ ውስጥ እና ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ውጭ የልማትና የበጎ አድራጎት ስራዎችን ያከናውናል፡፡
- በቤተክርስያኑ ውስጥ በሚከናወኑ የልማት ስረዎች ላይ እገዛ ያደርጋል፡፡
- በስሩ አራት ንኡሳን ክፍላት ይኖራሉ፡፡
የውስጥ እርዳታ ንኡስ ክፍል
- በሰንበት ትምርት ቤቱ ውስጥ የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው አባላትን ይለያል፡፡
- በሰንበት ትምህርት ቤቱ ውስጥ የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው አባላት ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- እራሳቸውን ማሻሻል እንዲችሉ የገቢ ማስገኛ መፍትሄዎችን ይቀርጻል፡፡
- ከአባላት የቁሳቁስና የገንዘብ እርዳታ ይሰበስባል፣ልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ዘዴዎችን ይቀርጻል፡፡
ውጫዊ እርዳታ ንኡስ ክፍል
- ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ውቺ ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች እርዳታ ያደርጋል፡፡
- በበዓላትን በልዩ ልዩ ጊዜያት ነዳያንን ይመግባል፣ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- አልባሳትና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- እስረኞችን እና ህመምተኞችን ይጎበኛል፤ አቅመ ደካሞችን በጉልበትና በገንዘብ ያግዛል፡፡
የገቢ ማስገኛ ንኡስ ክፍል
- በየጊዜው የሰንበት ትምህርት ቤቱን ገቢ ለማሳደግ ልዩ ልዩ ፕጀክችን ይቀርጻል፡፡
- የሰንበት ትምህርት ቤቱን ሱቅና ሌሎች የገቢ ምንጮችን ይከታተላል፡፡
- ለሽያች የሚቀርቡ ንዋያትን ያስመጣል፡፡
የግቢ ውስጥ ልማት ንኡስ ክፍል
- በደብሩ ቅጥር ግቢ ውስጥና በሰንበት ትምህርት ቤቱ ያሉ ልማታዊ ስራዎችን ያግዛል፡፡
- የችግኝ ተከላ መርሀግብሮችን ያዘጋጃል፣ይተክላል፣ ይንከባከባል፡፡
- ግንባታዎች ሲኖሩ አባላትን በማስተባበር የጉልበት እገዛ ያደርጋል፡፡
- የደብሩን ቅጥር ግቢ እና ቤተ መቅደሱን በየጊዜው ያጸዳል፡፡
- ልብሰ ተክህኖ፣የካህናት ልብስ እንዲታጠብ፣የካህናት ቤት እንዲጸዳ ያደርጋል፡፡
error: