Tesfahiwot


  • ተጠሪነቱ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት ይሆናል፡፡
  • በየደረጃው ላሉ ዓባላት መንፈሳዊ ትምህርትቶችን ያዘጋጃል፣ይሰጣል፣ይሰንዳል፡፡
  • ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን ይሰጣል፡፡
  • የትምህርትቶቹን እንቅስቃሴና አሰጣጥ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፡፡
  • ቤተ መጻሕፍቱን ያደራጃል ፤ይከታተላል፡፡
  • በስሩ አምስት ንኡሳት ክፍላት ይኖራሉ
ሄኖክ በቀለ ፡ የወቅቱ የክፍሉ ተጠሪ

  • ለየትምርቶች(ኮርሶች) እና ለየክፍላቱ መምህራንን ይመድባል፡፡
  • በሰንበት ትምህርት ቤቱ እውቅና ላላቸው ማህበራት መምህራንን ይመድባል፡፡
  • ተተኪ መምህራንን ለማስተማር ይመርጣል፤ ያሰለጥናል፡፡
  • ትምህርት የሚሰጡ መምህራንን ያወያያል፡፡
  • መምህራንን ክትትል ማድረግ

  • ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጃል፤ይሰበስባል፡፡
  • ትምህርቱ በተያዘለት የጊዜ መርሃግብር መከናወኑን ይከታተላል
  • ፈተና ከመምህራን ጋር ያዘጋጃል

  • ለልዩ ልዩ መርሀግብራት ትምህርቶችን ይቀርጸል፡፡
  • ስልጠናዎችን ያዘጋጃል ይሰበስባል፡፡
  • አውደ ርእዮችን፣በራሪ ወረቀቶችን፣መጽሐፍትን ያዘጋጃል፡፡
  • በማህበራዊ ድህረ ገጽ የሚለቀቁ ጽሑፎችን ያዘጋጃል ይገመግማል፡፡
  • ሳምንታዊ ጽሑፎችን በሰንበት ት/ቤቱ የማታወቂያ ቦርድ ላይ ይለጥፋል፡፡
  • ዶክመንተሪ ያዘጋጃል፡፡

  • ቤተመጻሕፍቱን በበላይነት ይቆጣጠራል፡፡
  • አስተናጋጆችን ይመድባል፡፡
  • መጽሐፍትን ከበጎ ፈቃደኞች ይሰበስባል እንዲሁም ግዢ እንዲፈጸም ያደርጋል፡፡
  • እንከን ያለባቸው መጽሐፍትን ይለያል፡፡
  • መጽሐፍትን ያውሳል፣የተዋሱት እንዲመለሱ ያደርጋል፡፡
  • የንባብ ልምድን ለማሳደግ (መጽሐፍት እንዲነበቡ) ልዩ ልዩ መርሃግብራትን ያዘጋጃል፡፡
  • የአባላትን የአስኳላ ት/ት ክትትል ማድረግ
  • በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ሚያመጡት ማበረታታት
  • በትምህርታቸው ደከም ያሉትን ማገዝ
  • አደረጃጀት ፈጥሮ የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ማስቻል

  • በሰንበት ትምህርት ቤቱ ዙሪያ ችግር ፈቺ ጥናቶችን ይሰራል፡፡
  • በቤተክርስቲያን ዙሪያ ችግር ፈቺ ጥናቶችን ይሰራል፡፡
  • ጥናቶቹ እንዲቀርቡ በማድረግ የውይይት መድረኮችን ያዘጋጃል፡፡
  • ጥናቶችን መሰረት በማድረግ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ፣ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን ይቀርጻል፡፡
error: