ንብረት ክፍል
- የሰንበት ትምህርት ቤቱን ንብረቶች ይቆጣጠራል፡፡
- የሰንበት ትምህት ቤቶችና የሌሎች ክፍላቶችን ቁልፍ ይይዛል፣ይከፍታል፣ይዘጋል፡፡
- በስሩ አምስት ንኡሳን ክፍላት ይኖራሉ፡-
ፅዳትና ደህንነት
- በሰንበት ትምህርት ቤቱ ያሉትን ንብረቶች ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡
- ልብሰ ስብሐትን እንዲሁም ሌሎች መገልገያ ቁሳቁሶችን አባላትን በማስተባበር እንዲጸዱ ያደርጋል፡፡
ንብረት ቆጠራና ምዝገባ (ግዢ)
- አዳዲስ ንብረቶችን ይመዘግባል፣ይረከባል፡፡
- ጠቅላላ የሰንበት ትምህርት ቤቱን ንብረቶች መዝግቦ ይይዛል
- በየ3 ወሩ ቆጠራ ያካሂዳል
- ለሰንበት ትምህርት ቤቱ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ግዚ ይፈጽማል
- ለተፈቀደላቸው ክፍላት የተገዙትን ንብረቶች ፈርሞ ያስረክባል፡፡
ልብሰ ስብሃት ቁጥጥር
- አገልግሎት በሚያስፈልግ ሰአት ለመዝሙር ክፍል አስፈርሞ ያስረክባል ይቀበላል
- የልብሰ ስብሐት እጥረት በሚገጥም ሰአት ግዢ እንዲፈጸም ለስራ አስፈጻሚ እንዲቀርብ ያደርጋል፡፡
እቃ ክፍል
- ክፍሉ ለአገልግሎት በሚፈለግበት ሰአት ክፍሉን ክፍት ያደርጋል፡፡
- ለማህበራትና ለተፈቀደላቸው አካላት በፎርም በማስፈረም እቃዎችን ያውሳል፡፡
- የሚከራዩ ንብረቶችን ክፍያ መፈጸሙን ሲያረግግጥ አስፈርሞ ይሰጣል፡፡
- በውሰት የወጡ እቃዎች በአግባቡ መመለሳቸውን ይከታተላል፣
- በአግባቡ ያልተመለሱ (ጉድለት የታየባቸውና ጉዳት የደረሰባቸው) እቃዎች ክፍያ እንዲፈጸም ወይም እንዲተኩ ያደርጋል፡፡
መዝገብ ቤት ንኡስ ክፍል
- በሰንበት ትምህርት ቤቱ ያሉ ደብዳቤዎችን ሁሉ ይሰንዳል፡፡
- የሰንበት ትምህርት ቤቱን ልዩ ልዩ መረጃዎችን ሁሉንም ያደራጃል፣ ይሰንዳል፡፡
- የሰንበት ትምህርት ቤቱ ማንኛውም ጽሑፋዊ ና ልዩ ልዩ ፋይሎችን ያደራጃል፣ይሰበስባል
- የየክፍላቱን መረጃዎች ሁሉ በመቀበል ዶክመንት ያደርጋል፡፡
- ክፍሎች ፋይል በሚፈልጉ ወቅት በማስፈረም ያውሳል ሲጨርሱ ይቀበላል፡፡
error: