አባላት ጉዳይ ክፍል
- የአባላትን ጉዳዮች ይከታተላል
- የሰንበት ትምህርት ቤቱን ግንኙነት ያጠናክራል፡፡
- በስሩ አምስት ንኡሳን ክፍላት ይኖሩታል
የአባላት መንፈሳዊና ማህበራዊ ሕይወት ክትትል ንኡስ ክፍል
- የንስሀ አባት የሌለቸውን እና ያላቸውን አባላት ይለያል
- የንስሀ አባት የሌላቸውን አባላት ከአባቶች ጋር እንዲገናኙ ያደርጋል፡፡
- የንስሀ ትምህርት ይሰጣል
- የወንድሞች እና የእህቶች ጉባኤ
- በየጊዜው የሕይወት ውይይቶችን ያዘጋጃል፡፡
- መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ይከታተላል፣ዝለት ለታየባቸው አባላት የምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡
- በሀዘን እና በደስታ ጊዜ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፡፡
- የቤተሰብ መዋቅሩን ይመራል, ይከታተላል።
የአባላት የጸሎት ንኡስ ክፍል
- ለሁሉም ክፍላት ቋሚ የጸሎት ሥርዓት ያዘጋጃል
- ጸሎት የሚያሳርጉ አገልጋዮችን ይመድባል
- ወቅታዊ የጸሎት መርሃግብራትን ይቀርጻል
- ለአባላት የጸሎት ሕይወታቸውን እንዲያሳድጉ ልዩ ልዩ እገዛዎችን ያደርጋል
- የሰንበት ትምህርት ቤቱን የዓመት ቋሚ የጸሎት መርሃግብር ያወጣል
- መርሃግብር ቀርጾ የሕብረት ጸሎት የሚደረግበትን መንገድ ለአባላት ያሰለጥናል (ያሳውቃል
- ለጸሎት የሚያስፈልጉ ግብአቶቸን (ቁሳቁሶችን…) ያሟላል
- ሰንበት ትምህርት ቤቱ ፈተና በገጠመው ጊዜ አባቶች(ገዳማውያን) ጸሎት እንዲይዙለት ያስተባብራል
- ሁሉም ክፍላት የጋራ የጸሎት ቀን እንዲኖራቸው ያደርጋል
- የሌሎች ሰንበት ት/ት ቤቶችን የጸሎት ልምድ ይካፈላል
አዲስ አባላትና የጠፉ አባላት ንኡስ ክፍል
- አዳዲስ አባላትን አስቀድሞ ያገኛል መሰረታዊ መረጃዎችን ያሳውቃል፡፡
- አዳዲስ አባላትን ይከታተላል፣ያወያያል፣ይደውላል..ወዘተ፡፡
- መርሀ ግብሮችን ያሳውቃል፡፡
- ከነባር አባላት ጋር ያስተዋውቃል፡፡
- ለአገልግሎት የደረሱ አባላትን ፎርም ያስሞላል፡፡
- ለአገልግሎት የደረሱ አባላትን ለቁጥጥር ክፍሉ ያስተላልፋል፡፡
- በየጊዜው የጠፉ አባላትን ይፈልጋል፡፡
- ጠፍተው የተመለሱ አባላት ወደ ቀድሞ አገልግሎታቸው እንዲመለሱሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡
- የአባላት መመዝገቢያ ፎርም ያዘጋጃል
- የአባላትን ፎርም በአግባቡ ይሰንዳል፣ ያደራጃል፡፡
ህዝብ ግንኙነት ንኡስ ክፍል
- የሰንበት ትምህርት ቤቱን የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮችንና ሌሎች የግኑኝነት መስመሮችን በስሩ ይቆጣጠራል፡፡
- ሰንበት ትምህርት ቤትን የሚመለከቱ መረጃዎችን ይሰበስባል ያሳውቃል፡፡
የስም ቁጥጥር ንኡስ ክፍል
- በሰንበት ት/ት ቤት ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ክፍሎች ላይ የየክፍሉን የስም ቁጥጥር የሚያደርግ ሰው ይመርጣል።
- የአባለትን መገኘት ይቆጣጠራል (ስም ይጠራል)
- በየጊዜው ቀሪ የሚያበዙና የጠፉ ልጆችን ስም ዝርዝር ለአዳዲስ አባላት ንኡስ ክፍል ያስተላልፋል፡፡
- ለበዓላት የሚዘምሩ/የሚያቀርቡ ዘማርያንን ይመርጣል።
የሰው ሀብት ንኡስ ክፍል
- ለአገልግሎት የሚሆን የሰው ኃይል ያበቃል
- ከጽ/ቤት ጋር በመሆን ለአገልግሎት የሚሆኑ አባላትን ያሰለጥናል
- ለአገልግሎት የሚሆን የሰው ኃይል ወደ ክፍላት ይመድባል
- ከክፍላት ወደ ክፍላት የሚደረግ ዝውውር በዚህ ክፍል ይፈጸማል
- እንዳስፈላጊነቱ ከክፍላት ተጠሪዎች ጋር በመነጋገር ከክፍላት ወደ ክፍላት አባላትን ያሸጋሽጋል