ኦዲትና ኢንስፔክሽን ክፍል
- በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚከወኑትን ተግባራት ይቆጣጠራል
- ተፈጻሚነታቸውን ይከታተላል
- በስሩ አራት ንኡሳን ክፍላት ይኖራሉ፡-
ቁጥጥር ንኡስ ክፍል
- በሰንበት ት/ት ቤት ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ክፍሎች ላይ የየክፍሉን ቁጥጥር የሚያደርግ ሰው ይመርጣል።
- የመርሀ ግራትን በጊዜ መጀመርና መጠናቀቅ ይቆጣጠራል፡፡
- በኪነጥበብ ክፍሉ እና በሌሎች ክፍላት የሚቀርቡትን ልዩ ልዩ መርሀግብራትን (ስነ ጽሑፍ ምሽት፣ቲያር፣አውደ ርእይ፣ስልጠናዎች… ወዘተ፡፡) ሰዓት ይቆጠራል፡፡
እቅድና ሪፖርት ክትትል ንኡስ ክፍል
- እቅዶችና ሪፖርቶች በጊዜያቸው መፈጸማቸውን ይከታተላል፡፡
- በክፍላት ስብሰባ ወቅት ተገቶ ስብሰባውን ይገመግማል።
- የስራ አስፈጻሚዎችን የስራ ሂደት ይከታተላል፡፡
ገንዘብና ንብረት ቁጥጥር
- የሰንበት ትምህርት ቤቱን ገቢና ወጪ ይቆጣጠራል
- የሰንበት ትምህርት ቤቱን ወጪ በእቅድ መሰረት መውጣቱን ይቆጣጠራል
- በሰንበት ትምህር ቤቱ ስር የተቀጠሩ ሰራተኞችን ክፍያ ይቆጣጠራል
- የወጪ ደረሰኝ ላይ ይፈርማል
- በየጊዜው ኦዲት ያደርጋል
- የሰንበት ትምህርት ቤቱን የበጀት አጠቃቀምና ንብረት አያያዝ ይከታተላል
ኢንስፔክሽን ንኡስ ክፍል
- ክፍላትን ተከታትሎ አቅጣጫ/ሃሳብ ይሰጣል
- ከክፍላት የየወሩን መርሃግብር ተቀብሎ ያለመደራረብ እንዲከናወኑ ይደለድላል
አርትኦት ንኡስ ክፍል
- በሰንበት ት/ት ቤቱ የሚዘጋጁት የኪነጥበብ፣መዝሙር፣ሕትመትና የሚዲያ ስራዎችን ይገመግማል
- በክፍሉ ያልታዩና ያልተፈቀዱ የኪነጥበብ፣መዝሙር፣ሕትመትና የሚዲያ ስራዎች እንዳይቀርቡ ያግዳል፡፡
error: