Tesfahiwot

የሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት

በጽሕፈት ቤቱ ስር ሰብሳቢ፣ምክትል ሰብሳቢና ጸሐፊ ይኖራሉ፡፡


ሰብሳቢ

  • የሰንበት ትምህርት ቤቱን የአባላትና የስራ አስፈጻሚ ጉባኤ ስብሰባ ይመራል፡፡
  • ከሰበካ ጉባኤ ጽሕፈት ቤትና ከሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን ያሳውቃል፣ያስፈጽማል፡፡
  • በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ሰንበት ትምህርት ቤቱን ወክሎ ይገኛል ፤ ካልተገኘም ሌሎች የስራ አስፈጻሚዎችን መወከል ይችላል፡፡
  • በስብሰባ ጊዜ ድምጽ እኩል ሲሆን ሰብሳቢው የወሰነው ውሳኔ ይጸድቃል፡፡
  • ሰንበት ትምህርት ቤቱን ወክሎ የተለያዩ ውሎችን ይዋዋላል፡፡
  • ከጸሐፊው ጋር በመነጋገር አጀንዳዎች እንዲያዙ ያደርጋል፡፡
  • ወደ ሰንበት ትምህርት ቤቱ የሚመጡ ደብዳቤዎችን ተቀብሎ ምላሽ ይሰጣል፤ይመራል፡፡
  • በከፍተኛ የሒሳብ ሰነዶች ላይ ይፈርማል፡፡
  • እስከ አንድ ሺ ብር ወጪ እንዲያደርግ ጸሐፊውን መወከል ይችላል፡፡
  • ዓመታዊ እቅዶችን ተወያይቶ ያጸድቃል ፡፡

የወቅቱ የሰንበት ት/ቤቱ ሰብሳቢ
ሳህለጊዮርጊስ ተስፋዬ


ምክትል ሰብሳቢ

  • ሰብሳቢው ባልተገኘበት ጊዜ ሙሉ የሰብሳቢውን ሀላፊነት ይወስዳል፡፡
  • ሰብሳቢው የሚሰራውን ስራ ያግዛል፡፡
  • የጽሕፈት ቤቱን እንቅስቃሴ ይከታተላል፡፡

የወቅቱ የሰንበት ት/ቤቱ ም/ሰብሳቢ
አዲሱ መኳንንት


ጸሐፊ

  • ከሰብሳቢው ጋር ሆኖ አጀንዳ ያዘጋጃል
  • በሰንበት ትምህርት ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤና በስራ አስፈጻው ጉባኤ ስብሰባ ላይ ቃለ ጉባኤ ይይዛል፤ ያስፈርማል፡፡
  • እቅዶችን በማስታወስ ተፈጻሚ ያደርጋል፡፡
  • ሰብሳቢውና ምክትል ሰብሳቢው በማይገኙበት ጊዜ ወክሎ ይሰራል፡፡
  • የስራ አስፈጻሚውን ውሳኔ ለሚመለከተው አካል በቃልና በጽሑፍ ያሳውቃል፡፡
  • የሰንበት ትምህርት ቤቱን ገቢና ወጪ ደብዳቤ በአግባቡ ይቆጣጠራል፤ ይሰንዳል ፡፡
  • የጽሕፈት ቤቱን ንብረቶች በአግባቡ ይይዛል ጉድለቶቹን አጥንቶ፤ ግዢ እንዲፈጸም ያደርጋል፡፡
  • ወደ ሰንበት ትምህርት ቤቱ የሚመጡ እንግዶችን ያስተናግዳል፤ጉዳያቸውን ያስፈጽማል፡፡
  • ደብዳቤዎችን ያዘጋጃል፤ የሰንበት ትምህርት ቤቱን አሰራር የሚያፋጥኑ ልዩ ልዩ ቅጾችን ያዘጋጃል፡፡
  • በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤና በሰንበት ትምህርት ቤቱ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ዓመታዊ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፡፡
  • በስብሰባ ጊዜ ሰብሳቢው በተወሰነው ጊዜ ጀምሮ እንዲፈጽም ያደርጋል (የስብሰባ ሰዓት ይቆጣጠራል) ፡፡
  • ሰብሳቢው ውክልና ሲሰጠው እስከ 1000 ብር ወጪ ማድረግ ይችላል፡፡
  • የክፍላት ተጠሪዎች ዕቅድ ና ሪፖርት በጊዜው እንዲያስገቡ ያደርጋል፡፡

የወቅቱ የሰንበት ት/ቤቱ ጸሐፊ
ዲ/ን ብርሃን ሰማው

error: