በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ቁጥራቸው ያልታወቀ በዋሻ የሚኖሩ መነኮሳት በታጣቂዎች ተገደሉ።
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኘው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የሚኖሩ መነኮሳት ሰኔ 15/ 2017 ዓ.ም. በታጣቂዎች የተገደሉ ሲሆን የተወሰኑ ታፍነው መወሰዳቸውን ገዳሙ ለማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ገልጿል።
ስለተገደሉ እና ታፍነው ስለተወሰዱ መነኮሳት ቁጥር እና ዝርዝር ጉዳይ አጣርተን መረጃዎችን የምናደርስ ይሆናል።
የካቲት 2016 ዓ.ም ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ በገዳሙ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መድረሱ የሚታወስ ነው።
Monks Killed
An unknown number of monks living in a cave at Zekuala Debre Kewakebet Abune Gebre Menfeskedus Monastery, Oromia Region, were killed by gunmen on June 22, 2025, while some were kidnapped, the monastery told to the MK Media Network.
We will provide information on the number and details of the monks who were killed and kidnapped.
It is worth noting that similar attacks have occurred on the monastery on several occasions, including in February 2024.
© MK Tv