28ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ከታህሳስ 24 – የካቲት 8 2018 ዓ.ም በተለያዩ መርሃግብራት ተከበረ
የተስፋሕይወት ሰንበት ት/ቤት 28ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ከታህሳስ 24 – የካቲት 8 2018 ዓ.ም በተለያዩ መርሃግብራት ተከበረ። 👉 ከታህሳስ 24 – 26 መንፈሳዊ አውደ ርዕይ – “ክብረ ክህነት”ን በተመለከተ። 👉 ጥር 2 (ጥናታዊ ጽሑፍ) – የወልቂጤ/ደ/ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የተስፋ ሕይወት ሰንበት ት/ት ቤት የአባላትን አገልግሎት ለማሳደግ የተደረገ የትግበራ ጥናት በሰንበት ት/ቤቱ ጥናትና ምርምር ክፍል
እጅግ አሳዛኝና ልብ የሚሰብር ኀዘን!!
በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በምንጃር ወረዳ አረርቲ ደብረ ገነት ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያ ላይ በአለው አዲሱ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለውስጥ ሥዕል መሳያ የተሰራው መወጣጫ የእንጨት ርብራብ መሰላል ሰዎች የሚሳለውን ሥዕል ለመጎብኘት ሲወጡ በመደርመሱ የሰዎች ሕይወት ማለፋንና በርካታ ምዕመናን ተጎድተዋል። ተጎጂዎች በአሁን ሰአት በምንጃር አረርቲ፣ በሞጆ ና በአዳማ የሕክምና እርዳታ እያገኙ ነው ! የሞቱ ወገኖቻችን ነፍሳቸውን በገነት
የመነኮሳት ግድያ
በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ቁጥራቸው ያልታወቀ በዋሻ የሚኖሩ መነኮሳት በታጣቂዎች ተገደሉ። በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኘው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የሚኖሩ መነኮሳት ሰኔ 15/ 2017 ዓ.ም. በታጣቂዎች የተገደሉ ሲሆን የተወሰኑ ታፍነው መወሰዳቸውን ገዳሙ ለማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ገልጿል። ስለተገደሉ እና ታፍነው ስለተወሰዱ መነኮሳት ቁጥር እና ዝርዝር
ቅድስት አፎምያና ባሕራን
ዲያቆን ተስፋዬ ቻይሰኔ ፲፩፤፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት ውድ የእግዚአብሔር ልጆች እንዴት አላችሁልን? በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዐዋጅ ታውጀው ከሚጾሙ አጽዋማት አንዱ የሆነው ጾመ ሐዋርያት የሚጾምበት ወቅት ላይ ነንና ይህን ጾም እንዴት እያሳለፋችሁት ነው? አባቶቻችንን ቅዱሳን ሐዋርያት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋን ከተቀበሉ በኋላ ወደ አገልግሎት ከመሄዳቸው በፊት ጾምን ጾመዋል፤ ይህን ጾም ምእመናን በየዓመቱ በዓለ ኀምሳ ከተከበረ ማግስት ጀምሮ እስከ
“ቃል ሥጋ ሆነ” (ዮሐ. ፩፥፲፬/1፥14)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ እንኳን ለጌታችን፣ ለአምላካችን እና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ። ይህ ቃልሥጋየመኾን ምስጢር፡- እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ በመወለዱ (ሰው በመሆኑ) [አምላክ ሰው የሆነበት] ልዩ ምስጢር፣ የሰው ልጅ በበደሉ ምክንያት ከመጣበት ሞት የዳነበት ምስጢር፣ ቤተ ክርስቲያናችን “ተዋሕዶ” የሚለውን ስያሜ ያገኘችበት፣ እኛም “ክርስቲያን” የተባልንበት ምስጢር፣ ሰማያዊው “ነገረ እግዚአብሔር” ለሰው ልጅ የተገለጠበት ምስጢር ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ምስጢረ ሥጋዌ ታላቅነት ሲናገር “የተነገረውን አስተውል፤ እግዚአብሔር