በወልቂጤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ተስፋ ሕይወት ሰ/ት/ቤት የመምህራን ግንዛቤ ማስጨበጫና የትምህርት ማስጀመሪያ ውይይት መስከረም 27/2018 ዓ.ም ተከናወነ። መ/ር ሳሙኤል ሰሎሞን ለሰ/ት ቤቱ መምህራን “ዓላማ ተኮር ልጆችን የማስተማር ሒደት” በሚል ርዕስ ስልጠና የሰጡ ሲሆን፥ የሰንበት ት/ት ቤቱ የትምህርት ክፍል ተጠሪ ዲ/ን ሄኖክ በቀለ ከመምህራኑ ጋር የትምህርት ሥርዓቱን በተመለተ ውይይት አድርገዋል፤ በተጨሪም የዓመቱን ዝርዝር የትምህርት መርሃግብርና የአሰራር ማሻሻያዎችን ለመምህራኑ ገለፃ አድርገዋል። የደብራችን አስተዳዳሪ መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ በዕለቱ ለተገኙ መምህራን ከመምህራኑ የሚጠበቁ ኃላፊነቶችን እንዲሁም ትውልዱ ላይ የሚታዩ ተስፋዎችን ተጠቅሞ ለቤተክርስቲያን በጎ ፍሬ ማፍራት እንደሚቻል አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመጨረሻም በ2017 የትምህርት ዘመን ሲያስተምሩ ለነበሩ መምህራን የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቶ የመርሃግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።


