Tesfahiwot

የተስፋሕይወት ሰንበት ት/ቤት 28ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ከታህሳስ 24  – የካቲት 82018 ዓ.ም በተለያዩ መርሃግብራት እንደሚከበር ተገለጸ። የምሥረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በተሰናዱ ልዩ ልዩ መርሃግብራት የሚከበር ሲሆን የመርሃግብራቱ ዝርዝርም በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት፡-

👉 ከታህሳስ 24 – 26 መንፈሳዊ አውደ ርዕይ – “ክብረ ክህነት”ን በተመለከተ።

👉 ጥር  2 (ጥናታዊ ጽሑፍ) – የወልቂጤ/ደ/ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የተስፋ ሕይወት ሰንበት ት/ት ቤት የአባላትን አገልግሎት ለማሳደግ የተደረገ የትግበራ ጥናት በሰንበት ት/ቤቱ ጥናትና ምርምር ክፍል ይቀርባል።

👉 ጥር 17 – የወላጆች ጉባኤ :- ወላጆች የልጆቻቸውን ሰ/ት/ቤት ምሥረታ በልዩ ልዩ መርሃግብራት የሚያከብሩበት።

👉 የካቲት 1 – የአባላት ጉዞ

👉 የካቲት 8 – የአባላትጉባኤ :- ነባርና አዳዲስ አባላት የሚተዋወቁበት፣ የሰንበት ት/ቤቱ ታሪክ የሚዘከርበትና የምሥረታው የማጠቃለያ ልዩ መርሃግብር።

በእነዚህ ምዕመናንን እንዲሁም አባላትን በሚያሳትፉ መርሃግብራት ከታህሳስ24እስከየካቲት8 ድረስ አብረውን እንዲያከብሩ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Leave A Comment

error: