Tesfahiwot

በከተራ ዕለት በከተማው ከሚገኙ አድባራት  ከየመንበረ ክብራቸው ተነስተው ወደ  ጥምቀተ ባህር የተጓዙ ሲሆን በባህረ ጥምቀት የሀገረስብከታችን ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መሥራችና የበላይ ኃላፊ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ሰብሳቢ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ትምህርተ ወንጌል ዝማሬ እንዲሁም መልዕክታት ተላልፈው ጉዞው ተጠናቋል።

በሌሊት አገልግሎት ማህሌት ቅዳሴው ተከናውኖ በጥምቀት ዕለት በጠዋቱ መርሃግብር  ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የሀገረስብከት የስራ ሃላፊዎች የደብራት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የመንግስት ኃላፊዎች በተገኙበት ሥርዓተ ጥምቀቱ ተከናውኗል።

በመጨረሻም በዓሉ ከዋዜማው ጀምሮ በድምቀት ተከብሮ ከቅዱስ ሚካኤል ታቦት ውጭ ሌሎች ታቦታት  ወደ መንበረ ክብራቸው ከተማውን እየባረኩ ተጉዘዋል።

የመጨረሻ መዳረሻ በነበረው በደብራችን በወልቂጤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በብጹዕነታቸው ቃለምዕዳን ተጠናቋል።

Leave A Comment

error: