Tesfahiwot

የተስፋሕይወት ሰንበት ት/ቤት 29ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ከህዳር 6 እስከ ታኃሣሥ 4 2019 ዓ.ም በተለያዩ መርሃግብራት እንደሚከበር ተገለጸ።

የምሥረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በተሰናዱ ልዩ ልዩ መርሃግብራት የሚከበር ሲሆን የመርሃግብራቱ ዝርዝርም በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት፡-

👉 ህዳር 6 – የበገና ምሽትና ለ10ኛ ዙር በሰንበት ት/ቤታችን ሲሰጥ የነበረውን የበገና ትምህርት ያጠናቀቁ ተማሪዎች ምርቃት

👉 ህዳር 13 – የወላጆች ጉባኤ :- ወላጆች የልጆቻቸውን ሰ/ት/ቤት ምሥረታ በልዩ ልዩ መርሃግብራት የሚያከብሩበት።

👉 ህዳር 19 እና 20 – በህክምና ሙያ ላይ ያሉ የሰንበት ት/ቤታችን አባላት ለምዕመናን የነጻ ህክምና አገልግሎት የሚሰጡበት ቀን

👉 ህዳር 20 – በአዲስ አበባ የሚገኙ የሰ/ት/ቤታችን አባላት በመንፈሳዊ ጉዞ የምስረታ በዓል የሚያከብሩበት መርሃግብር።

👉 አውደርዕይ – ከህዳር 25 – 27

👉 ታኃሣሥ 4 – የአባላት ጉባኤ :- ነባርና አዳዲስ አባላት የሚተዋወቁበት፣ የሰንበት ት/ቤቱ ታሪክ የሚዘከርበትና የምሥረታው የማጠቃለያ ልዩ መርሃግብር።

በእነዚህ ምዕመናንን እንዲሁም አባላትን በሚያሳትፉ መርሃግብራት ከህዳር 6 እስከ ታኃሣሥ 4 2019 ዓ.ም ድረስ አብረውን እንዲያከብሩ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Leave A Comment

error: