28ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ከታህሳስ 24 – የካቲት 8 2018 ዓ.ም በተለያዩ መርሃግብራት ተከበረ
የተስፋሕይወት ሰንበት ት/ቤት 28ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ከታህሳስ 24 – የካቲት 8 2018 ዓ.ም በተለያዩ መርሃግብራት ተከበረ። 👉 ከታህሳስ 24 – 26 መንፈሳዊ አውደ ርዕይ – “ክብረ ክህነት”ን በተመለከተ። 👉 ጥር 2 (ጥናታዊ ጽሑፍ) – የወልቂጤ/ደ/ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የተስፋ ሕይወት ሰንበት ት/ት ቤት የአባላትን አገልግሎት ለማሳደግ የተደረገ የትግበራ ጥናት በሰንበት ት/ቤቱ ጥናትና ምርምር ክፍል
የ2018 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በወልቂጤ ከተማ በድምቀት ተከበረ
በከተራ ዕለት በከተማው ከሚገኙ አድባራት ከየመንበረ ክብራቸው ተነስተው ወደ ጥምቀተ ባህር የተጓዙ ሲሆን በባህረ ጥምቀት የሀገረስብከታችን ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መሥራችና የበላይ ኃላፊ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ሰብሳቢ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ትምህርተ ወንጌል ዝማሬ እንዲሁም መልዕክታት ተላልፈው ጉዞው ተጠናቋል። በሌሊት አገልግሎት ማህሌት ቅዳሴው ተከናውኖ
28ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል
የተስፋሕይወት ሰንበት ት/ቤት 28ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ከታህሳስ 24 – የካቲት 82018 ዓ.ም በተለያዩ መርሃግብራት እንደሚከበር ተገለጸ። የምሥረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በተሰናዱ ልዩ ልዩ መርሃግብራት የሚከበር ሲሆን የመርሃግብራቱ ዝርዝርም በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል። በዚህም መሰረት፡- 👉 ከታህሳስ 24 – 26 መንፈሳዊ አውደ ርዕይ – “ክብረ ክህነት”ን በተመለከተ። 👉 ጥር 2 (ጥናታዊ ጽሑፍ) – የወልቂጤ/ደ/ብሥራት ቅዱስ
የመምህራን ግንዛቤ ማስጨበጫና የትምህርት ማስጀመሪያ ውይይት
በወልቂጤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ተስፋ ሕይወት ሰ/ት/ቤት የመምህራን ግንዛቤ ማስጨበጫና የትምህርት ማስጀመሪያ ውይይት መስከረም 27/2018 ዓ.ም ተከናወነ። መ/ር ሳሙኤል ሰሎሞን ለሰ/ት ቤቱ መምህራን “ዓላማ ተኮር ልጆችን የማስተማር ሒደት” በሚል ርዕስ ስልጠና የሰጡ ሲሆን፥ የሰንበት ት/ት ቤቱ የትምህርት ክፍል ተጠሪ ዲ/ን ሄኖክ በቀለ ከመምህራኑ ጋር የትምህርት ሥርዓቱን በተመለተ ውይይት አድርገዋል፤ በተጨሪም የዓመቱን ዝርዝር የትምህርት መርሃግብርና
ተስፋሕይወት ሰንበት ት/ቤትሽ በአንቺ ትኮራለች!
የሰንበት ት/ቤታችን የ12ኛ ክፍል አባል ተማሪ ሄላ ፈለቀ በዘንድሮው ሀገር አቀፍ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና 546 ከፍተኛ ውጤት በማምጣትሽ እንኳን ደስ አለሽ።
የአዲስ ዓመት በዓል በተስፋሕይወት ሰ/ት/ቤት በድምቀት ተከበረ።
የ2018 አዲስ ዓመት የበዓል ልዩ መርሃግብር እሁድ መስከረም 04 2018 ዓ.ም ተካሄዷል። በመርሃግብሩ የተለያዩ የበዓል መርሃግብራት የቀረቡ ሲሆን የደብራችን አስተዳዳሪ መጋቤ ሐዲስ አባ ገብረኢየሱስ (ቆሞስ) ትምህርተ ወንጌልና ቡራኬ ሰጥተዋል። እንዲሁም በበዓሉ ዕለት በአገልግሎት ተጠምደው ለምዕመናን በየቤቱ በመሄድ እንኳን አደረሳችሁ ላሉ የሰንበት ት/ቤታችን አባላት ምስጋና ቀርቧል።
ለአዲሱ ዓመት እንኳን አደረስዎ
የወልቂጤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተስፋሕይወት ሰንበት ት/ ቤት አባላት መስከረም 1 2018 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ሣልሳይ የጉራጌ ሀ/ስብከት ሊቀጳጳስን በመንበረ ጵጵስናቸው ተገኝተው እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረስዎ በማለት ቡራኬ ተቀብለዋል።
ዝክረ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ተካሄደ
ሐምሌ 23/11/2017ዓ.ም የሊቁ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ የእረፍታቸው መታሰቢያ መርሃግብር ተካሄዷል። በመርሃግብሩ ላይ ሊቁ ሕይወታቸውንና አበርክቷቸው የተዳሰሰ ሲሆን “ኰኵሐ ሃይማኖት” መጽሐፍ ተዳሷል። እንዲሁም ቅኔያቸውና ትምህርታቸውን የተመለከተ ሰፊ ዳሰሳ ቀርቧል። የወልቂጤ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተስፋሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓለ ንግሥ
የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓለ ንግሥ በወልቂጤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሐምሌ 19 2017 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ተከበረ።