የሐምሌ ገብርኤል ሥርዓተ ማህሌት
እንኳን አደረሳችሁ ! የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል ሥርዓተ ማህሌት በወልቂጤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሐምሌ 18 2017
የሽልማት መርሃግብር
በ2017 ዓ.ም የወልቂጤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተስፋሕይወት ሰ/ት/ቤት ሕፃናትን ጨምሮ ከ1-12ኛ ክፍል በተዘረጋው ስርዓተ ት/ት መሠረት እንዲሁም መስማት የተሳናቸውን ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ ሲያስተምር ቆይቶ የዓመቱን ማጠቃለያ መርሃግብር ሐምሌ 13 2017 ዓ.ም የደብራችን አስተዳዳሪ መጋቤ ሐዲስ አባ ገ/ኢየሱስ (ቆሞስ) ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንዲሁም የተማሪ ወላጆች በተገኙበት ተከናውኗል ፡፡ በመርሃግብሩ ላይ በሰንበት ት/ቤታችን ከየክፍሉ እና ከአጠቃላይ
የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ንግሥ
በጅማ ሀገረ ስብከት የቁምቢ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ንግሥ። ሰንበት ትምህርት ቤታችንም በቁምቢ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተገኝቶ በዓሉን በድምቀት እንዲህ አክብሯል።
የጸሎትና የስልጠና መርሃግብር
በዘንድሮ ዓመት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የጸሎት መርሃግብርና የስነ ልቦና ዝግጅትን በተመለከተ ስልጠና ሰንበት ት/ቤታችን ከማህበረቅዱሳን ወልቂጤ ወረዳ ማዕከል ጋር በመተባበር ሰኔ 15 2017 ዓ.ም ተሰጥቷል።
የተማሪዎች ምርቃት
በወልቂጤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተስፋ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት በ2017 ዓ.ም ለምዕመናን ሲሰጥ የነበረውን የቀዳማይ ኮርስ ያጠናቀቁ ተማሪዎች ሰኔ 15 2017 ዓ.ም ተመረቁ።