ተስፋሕይወት ሰንበት ት/ቤት
የአገልግሎት ክፍላት
ተስፋሕይወት ሰንበት ት/ቤት
የትምህርት(የማስተማርያ) ክፍላት
የሥርዓተ ትምህርት ክፈላት፦ ከቅድመ መደበኛ-12ኛ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በትግበራ ላይ በሚገኘው ሥርዓተ ትምህርት መሠረትከቅድመ መደበኛ እስከ12ኛ ክፍል ትምህርት በመሰጠት ላይ ይገኛል።
የመደበኛ ትምህርት፦ ከቀዳማይ-ሳልሳይ አቢይ ጉባኤ ክፍል
በተለያዩ ምክንያቶች በሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሥርዓተ ት/ት ውስጥ ተካተው መማር ላልቻሉ ምእመናን ወደ ሰንበት ትምህርት ቤቱ መደበኛ አገልግሎት ከመግባታቸወና የአባልነት ፎርም ከመሙላታቸው አስቀድሞ ሊማሯቸው ይገባል ተብለው የሚታሰቡና በየደራጃው የሚሰጡ መሠረታዊ የቤተክርስቲያን ኮርሶችን ያካተተ ነው።